Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እና​ን​ተም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ስለ እና​ንተ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ስለ እና​ንተ የተ​ዋጋ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ሲል በእነዚህ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረገውን ማንኛውንም ነገር እናንተው ራሳችሁ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋላችሁ ራሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እናንተም ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ ጌታ አምላካችሁ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አምላካችን እግዚአብሔር እናንተን ለመርዳት በእነዚህ ሕዝቦች ላይ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለ እናንተ ተዋግቶላችኋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እናንተም አምላካቸሁ እግዚአብሔር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፥ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 23:3
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እና​ንተ ይዋ​ጋል፤ እና​ን​ተም ዝም ትላ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው።


በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን፥ እንደ ንስር ክን​ፍም እንደ ተሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ወደ እኔም እን​ዳ​መ​ጣ​ኋ​ችሁ አይ​ታ​ች​ኋል።


እሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ከፍ ያለ​ውን ኮረ​ብታ ሁሉ፥ ቅጠ​ላ​ማ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚ​ያም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ሠዉ፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ኝን፤ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ በዚ​ያም ደግሞ ጣፋ​ጩን ሽታ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አፈ​ሰሱ።


ዓይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም፦ እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ።


በፊ​ታ​ችሁ የሚ​ሄ​ደው አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በግ​ብፅ ምድር እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ሁሉ፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮ​አ​ችሁ ይዋ​ጋል፤


ከእ​ና​ንተ ጋር የሚ​ሄድ፥ ያድ​ና​ች​ሁም ዘንድ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ስለ እና​ንተ የሚ​ወጋ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


“በል​ብ​ህም፦ እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ከእኔ ይልቅ ይበ​ዛ​ሉና አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እን​ዴት እች​ላ​ለሁ? ብለህ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤


ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል፤ ስማ​ቸ​ው​ንም ከዚያ ቦታ ያጠ​ፋል፤ እስ​ክ​ታ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ማንም ከፊ​ትህ ይቆም ዘንድ አይ​ች​ልም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ይዋጋ ነበ​ርና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ውን ቃል የሰ​ማ​በት እን​ደ​ዚያ ያለ ቀን ከዚ​ያም በፊት ከዚ​ያም በኋላ አል​ነ​በ​ረም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረን ስለ እና​ንተ የሚ​ዋጋ እርሱ ነውና ከእ​ና​ንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳ​ድ​ዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos