ኢያሱ 22:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ከመሆኑ በፊት የእስራኤል ሕዝብ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን በገለዓድ ምድር ወደሚገኙት ወደ ሮቤል፥ ወደ ጋድና በምሥራቅ ወደሚኖሩት የምናሴ ነገዶች ሕዝብ ላኩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም እስራኤላውያን የካህኑ የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን በገለዓድ ምድር ወደሚኖሩት ወደ ሮቤልና ወደ ጋድ እንዲሁም ወደ ምናሴ ነገድ እኩሌታ ላኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ላኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ የካህኑ የአሮንን ልጅ የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ላኩ። |
ሙሴም ከየነገዱ አንዳንድ ሺህ ሰው በካህኑ በአልዓዛር ልጅ በፊንሐስ መሪነት ወደ ጦርነት ላካቸው፤ ፊንሐስም ከመቅደሱ አንዳንድ ንዋየ ቅድሳትንና ለጦርነት መቀስቀሻ (ክተት) የሚሆን መለከት በእጁ ይዞ ነበር።
የአሮን ልጅ አልዓዛርም ሞተ፤ በጊብዓም ተቀበረ፤ እርስዋም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኝና ለልጁ ለፊንሐስ መኖሪያ የተሰጠች ትንሽ ከተማ ናት።
የእስራኤል ነገዶች በመላው በብንያም ግዛት ተዘዋውረው እንዲህ የሚል ቃል የሚናገሩትን መልእክተኞች ላኩ፥ “ይህ የፈጸማችሁት ክፉ ነገር ምንድን ነው?
በዚያን ዘመን የአሮን ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ስለ ነበረ እግዚአብሔርን ጠየቀ፦ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመውጋት እንደገና እንውጣን ወይስ እንቅር” ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ነገ በእነርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጁ አደርጋለሁና ሂዱና ውጉአቸው!” አለ።