ኢያሱ 21:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቂብጻይምና ቤትሖሮን የተባሉት ከግጦሽ መሬቶቻቸው ጋር ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂብጻይሞና ቤትሖሮን ከነመሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቂብጻይምንና መሰማሪያዋን፥ ቤት-ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቄብጻይምንና መሰማርያዋን፥ ቤቶሮንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቂብጻይምንና መሰምርያዋን፥ ቤትሖሮንንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። |
እግዚአብሔርም በእስራኤል ሠራዊት ፊት አሞራውያን በድንጋጤ እንዲሸበሩ አደረገ፤ እስራኤላውያንም እነርሱን በገባዖን ዐረዱአቸው፤ የቀሩትንም በቤትሖሮን በኩል እስከ ተራራው መተላለፊያ ቊልቊለት እስከ ዐዜቃና እስከ ማቄዳ ድረስ አሳደዱአቸው።
ከዚያም በምዕራብ በኩል ወደሚገኙት ወደ ያፍሌጣውያን ይዞታ በመዝለቅ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ይደርሳል፤ ከዚያም ወደ ጌዜር ያልፍና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል።
ለእነርሱም የተሰጡት አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ሴኬምና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚገኙት የግጦሽ መሬቶችዋ፥ ጌዜር፥