ኢያሱ 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ ከሌዊ ነገድ የአሮን ዘሮች ለሆኑት ለቀዓት ወገኖች ተሰጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ከተሞች የሌዊ ልጆች፣ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለአሮን ዝርያዎች ተመደቡ፤ ይህም የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣላቸው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። |
በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርይትአርባቅ የምትባለውን ከተማ፥ በዙሪያዋ ካለው የግጦሽ መሬት ጋር ሰጡአቸው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፤ ይህም አርባቅ የዐናቅ አባት ነበር።
የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ጐሣ ወጣ፤ ከሌዊ ነገድ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተከፋፈለ፤ እነዚህም ከተሞች የተወሰዱት ከይሁዳ፥ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ይዞታዎች ነበር፤