ኢያሱ 18:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸው ድንበር በደቡብ በኩል ቀድሞ ሎዛ ተብላ ትጠራ ወደነበረችው ወደ ቤትኤል ይወጣና በታችኛው ቤትሖሮን ተራራ በኩል ወደ ዐጣሮትአዳር ይወርዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ደግሞ ወደ ደቡብ ሎዛ ማለት ወደ ቤቴል ተረተር ይሻገርና በታችኛው ቤትሖሮን በስተ ደቡብ ባለው ተራራ በኩል አድርጎ ወደ አጣሮት አዳር ይወርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል በሎዛ አቅጣጫ ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ወገን አለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ዐለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤቶሮን ደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ ማአጣሮቶሬክ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ አለፈ፥ ድንበሩም በታችኛው ቤትሖሮን በደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ አጣሮትአዳር ወረደ። |
አሞራውያን በመተላለፊያው ቊልቊለት ከእስራኤላውያን ሠራዊት በሚሸሹበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር እስከ ዐዜቃ ድረስ ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ ስለዚህም እስራኤላውያን ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶው ድንጋይ የሞቱት እጅግ ብዙዎች ነበሩ።
ይኸው ድንበር በሌላም አቅጣጫ ከዚህ ተራራ በስተ ምዕራብ ወደ ደቡብ በመታጠፍ የይሁዳ ነገድ ይዞታ ወደ ሆነችው ከተማ ወደ ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪም ያልፋል፤ ይህም በምዕራብ በኩል የሚገኘው ድንበር ነው፤