ሰዎች መጥተው ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ “በአንተ ላይ አደጋ ለመጣል እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ከሙት ባሕር ባሻገር ካለው ከኤዶም ምድር መጥቶብሃል፤ እነሆ ሐጸጾንታማርን ቀደም ሲል በድል አድራጊነት ይዘዋል” ሲሉ ነገሩት፤ (ሐጸጾንታማር የዔንገዲ ሌላ መጠሪያ ስሙ ነው፤)
ኢያሱ 15:62 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኒብሻን፥ የጨው ከተማና ዔንገዲ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች ያጠቃልላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኒብሻን፣ የጨው ከተማና ዓይንጋዲ፤ እነዚህም ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፤ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናፍላዛንና ከተሞቻቸው፥ ሳዶን፥ አቃዴስ፥ ሰባት ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኒብሻን፥ የጨው ከተማ፥ ዓይንጋዲ፥ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ሰዎች መጥተው ለንጉሥ ኢዮሣፍጥ “በአንተ ላይ አደጋ ለመጣል እጅግ ብዙ የሆነ ሠራዊት ከሙት ባሕር ባሻገር ካለው ከኤዶም ምድር መጥቶብሃል፤ እነሆ ሐጸጾንታማርን ቀደም ሲል በድል አድራጊነት ይዘዋል” ሲሉ ነገሩት፤ (ሐጸጾንታማር የዔንገዲ ሌላ መጠሪያ ስሙ ነው፤)
ከዔንገዲ ጀምሮ እስከ ዔንዔግላይም ድረስ ዓሣ አጥማጆች ይቆማሉ፤ ያም ቦታ መረቦች የሚዘረጉበት ቦታ ይሆናል፤ በሜዲትራኒያን ባሕር እንደሚገኘው ዐይነት በዚህም ልዩ ልዩ ዓሣ ይገኛል።
ነገር ግን የይሁዳ ሕዝብ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ማባረር አልቻሉም፤ ስለዚህም ኢያቡሳውያን እስከ አሁን ድረስ በኢየሩሳሌም ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ይኖራሉ።