በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።
ኢያሱ 15:57 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃይን፥ ጊብዓና ቲምና ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥር ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ያጠቃልላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃይን፣ ጊብዓና ተምና ናቸው፤ እነዚህም ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፤ ዐሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጋባ፥ ተምና፥ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥ ቃይን፥ ጊብዓ፥ ተምና፥ አሥር ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።
ይህችው ሴት ዘግየት ብላ ሌሎች ሁለት ወንዶች ልጆችን እነርሱም የማድማናን አባት ሳፋንና የማክቢናና የጊብዓን አባት ሻዋን ወለደችለት። ካሌብ በተጨማሪ ዓክሳ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው።
ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል።