ዖዝያ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ የጋትን፥ የያብኔንና የአሽዶድን ከተማዎች ቅጽሮችን አፈራረሰ፤ በአሽዶድ አጠገብና በቀሩትም የፍልስጥኤም ግዛት ውስጥ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ።
ኢያሱ 15:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአሽዶድም አቅራቢያ ከዔቅሮን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር የተሠሩ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ከአቃሮን በስተ ምዕራብ በአሽዶድ አካባቢ ያሉ ሰፈሮችና መንደሮቻቸው ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕሩ ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአቃሮንና ከጌምና ጀምሮ በአሴዶት አቅራቢያ ያሉ ሁሉና መንደሮቻቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአቃሮንም ጀምሮ እስከ ባሕር ድረስ በአዛጦን አጠገብ ያሉት ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር። |
ዖዝያ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ የጋትን፥ የያብኔንና የአሽዶድን ከተማዎች ቅጽሮችን አፈራረሰ፤ በአሽዶድ አጠገብና በቀሩትም የፍልስጥኤም ግዛት ውስጥ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ።
እንዲሁም በግብጽ ወሰን እስከሚገኘው ወንዝና እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ድረስ የሚደርሱ ታናናሽ ከተሞችና መንደሮች ያሉአቸው አሽዶድና ጋዛ ተብለው የሚጠሩ ከተሞች ነበሩ።