ኢያሱ 15:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልባዎት፥ ሺልሒም፥ ዓይንና፥ ሪሞን ተብለው የሚጠሩት በድምሩ ኻያ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙት ታናናሽ ከተሞችንም ሁሉ ያጠቃልላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባዎት፣ ሺልሂም፣ ዓይንና ሪሞን ናቸው፤ በአጠቃላይም ከተሞቹና መንደሮቻቸው ሃያ ዘጠኝ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዐይን፥ ሪሞን፤ ሀያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላቦስ ሳሌ፥ ኤርሞትም ሃያ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልባዎት፥ ሺልሂም፥ ዓይን፥ ሪሞን፥ ሀያዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
በሰሜን ከጌባዕ አንሥቶ ኢየሩሳሌምን በደቡብ በኩል አልፎ እስከ ሪሞን ድረስ ያለው አውራጃ ደልዳላ ይሆናል፤ ኢየሩሳሌም በዙሪያዋ ካለው ምድር በላይ ከፍ ትላለች፤ ከተማይቱም ከብንያም በር አንሥቶ በቀድሞው በር አቅጣጫ እስከ ማእዘን በር እንዲሁም ከሐናንኤል ግንብ አንሥቶ እስከ ቤተ መንግሥቱ ወይን መጭመቂያው ድረስ ከፍ በማለት ጸንታ ትኖራለች።
ዓይን ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ዩጣና ከግጦሽ መሬትዋ ጋር፥ ቤትሼሜሽ ከግጦሽ መሬትዋ ጋር ከይሁዳና ከስምዖን ምድር ተከፍለው የተሰጡ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው።