ይህችው ሴት ዘግየት ብላ ሌሎች ሁለት ወንዶች ልጆችን እነርሱም የማድማናን አባት ሳፋንና የማክቢናና የጊብዓን አባት ሻዋን ወለደችለት። ካሌብ በተጨማሪ ዓክሳ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው።
ኢያሱ 15:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የካሌብ ወንድም ከሆነው ከቀናዝ የተወለደው ዖትኒኤል ያችን ከተማ ወግቶ ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ከተማዪቱን ያዛት፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፤ ስለዚህ ካሌብ ልጁን ዓክሳንን አጋባው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፤ ልጁን አክሳንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካሌብ ወንድም የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል ያዛት፥ ልጁንም ዓክሳን አጋባው። |
ይህችው ሴት ዘግየት ብላ ሌሎች ሁለት ወንዶች ልጆችን እነርሱም የማድማናን አባት ሳፋንና የማክቢናና የጊብዓን አባት ሻዋን ወለደችለት። ካሌብ በተጨማሪ ዓክሳ ተብላ የምትጠራ አንዲት ሴት ልጅ ነበረችው።
ቀናዝም ዖትኒኤልና ሠራያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዖትኒኤልም ሐታትና መዖኖታይ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤
ይህም የእግዚአብሔር ውሳኔ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸው ከታዘዙት ከቀኒዛዊው ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ማንኛውንም ሰው የሚያጠቃልል ነው። ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው የተገኙት እነርሱ ብቻ ናቸው።
አንድ ቀን ከይሁዳ ነገድ የሆኑ ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከእነርሱ አንዱ የቀኒዛዊው የይፉኔ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “በቃዴስ በርኔ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ስለ አንተና ስለ እኔ የተናገረውን ታውቃለህ፤
ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብ ታናሽ ወንድም ልጅ የሆነውን የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን አስነሣቸው።