ኢያሱ 13:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግዛታቸውም ማሕናይምንና ባሳንን ሁሉ ያጠቃልላል፤ ይህም ባሳን መላውን የባሳን ንጉሥ የዖግን ግዛት እንዲሁም በባሳን በተለይ ያኢር ተብላ በምትጠራው ስፍራ የሚገኙትን ሥልሳ ከተሞች ሁሉ ይጨምራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንበራቸው ከመሃናይም አንሥቶ ባሳንን በሙሉ ይጨምርና፣ በባሳን ያሉትን ስድሳ የኢያዕር ከተሞች ሁሉ ይዞ የባሳን ንጉሥ የዐግን ግዛት ሁሉ የሚያካትት ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግዛታቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበራቸውም ከመሐናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥ የገለዓድም እኩሌታ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበራቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥ የገለዓድም እኩሌታ፥ |
ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ተከትለው ሄዱ፤ የባሳን ንጉሥ ዖግ በኤድረዒ ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም ከመላ ሠራዊቱ ጋር ወጣ።
በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ የዖግ ግዛቶች የሆኑትን በደጋ የሚገኙትን ሳለካና ኤድረዒ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና እንዲሁም የገለዓድንና የባሳንን አውራጃዎች ሁሉ ያዝን።
በዚያኑ ጊዜ ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም፤ በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ ዖግ በአርጎብ ግዛት ያስተዳድራቸው የነበሩትን ሥልሳ ከተሞች ወሰድን።
ከጋድ ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥