ቤትየሺሞት፥ ባዓልመዖንና ቂርያታይም የተባሉት ዝነኞቹ ከተሞች ሳይቀሩ የሞአብ ጠረፍ የሚጠበቅባቸው ከተሞችን ሁሉ በጠላት እንዲመቱ አደርጋለሁ።
ኢያሱ 13:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤትፐዖር፥ ከፒስጋ ተራራ በታች ያለው ረባዳ ምድርና ቤትየሺሞት ተብለው የሚጠሩትን ሁሉ ይጨምራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤተ ፌጎርን፣ የፈስጋን ሸንተረሮችና ቤትየሺሞትን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤተ ፌጎር፥ የፈስጋ ተዳፋት መሬት፥ ቤትየሺሞት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤተ ፌጎር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤትሲሞት፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤተ ፌጎር፥ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለው ምድር፥ ቤትየሺሞት፥ |
ቤትየሺሞት፥ ባዓልመዖንና ቂርያታይም የተባሉት ዝነኞቹ ከተሞች ሳይቀሩ የሞአብ ጠረፍ የሚጠበቅባቸው ከተሞችን ሁሉ በጠላት እንዲመቱ አደርጋለሁ።
በስተ ምዕራብ በኩል ያለው ግዛታቸው አራባን ዮርዳኖስንና በአካባቢው ያለውን ምድር ያጠቃልላል፤ በስተምሥራቅ በኩል ከገሊላ ባሕር በፒስጋ ተራራ ግርጌ እስካለው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ይደርሳል።
እነዚህንም ያወጀው በዮርዳኖስ ማዶ በቤትፔዖር ሸለቆ ፊት ለፊት የአሞራውያን ንጉሥ በነበረው በሐሴቦን በነገሠውና ሙሴና እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ ጊዜ ተዋግተው ባሸነፉት በሲሖን ምድር ነው።
እርሱም በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ሸለቆ የገሊላ ባሕር ድረስ፥ በቤት የሺሞት አቅጣጫ እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ ከጨው ባሕር ወደ ደቡብ እስከ ፒስጋ ተራራ ታች ድረስ ያለውን ያጠቃልላል።
በደጋማው አገር የሚገኙትን ከተሞችና መኖሪያውን በሐሴቦን አድርጎ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖንን ግዛት ሁሉ ይጨምራል። ሙሴም ንጉሥ ሲሖንንና የምድያም መሪዎች የነበሩትን፥ ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ድል ነሣ፤ እነዚህ ሁሉ ምድሪቱን የሚያስተዳድሩት የንጉሥ ሲሖን ገባሮች በመሆን ነበር።