ኢያሱ 13:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገና ያልተያዙትም እነዚህ ናቸው፦ የፍልስጥኤምና የገሹር ግዛት በሙሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚቀረውም ምድር ይህ ነው፤ “እርሱም የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳይያዝ የቀረውም ምድር ይህ ነው፥ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረችውም ምድር ይህች ናት፤ የፍልስጥኤማውያን፥ የጌሴርያውያንና የከነዓናውያን ሀገር ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረችውም ምድር ይህች ናት፥ የፍልስጥኤማውያንና የጌሹራውያን አገር ሁሉ፥ |
በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
እኔ አገልጋይህ በሶርያ በምትገኘው በገሹር በኖርኩበት ጊዜ ‘ወደ ኢየሩሳሌም ብትመልሰኝ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ’ ብዬ ለእግዚአብሔር ስእለት ተስዬ ነበር።”
ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢጌል የተወለደው ኪልአብ፥ ሦስተኛው ታልማይ ተብሎ የሚጠራው የገሹር ንጉሥ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥
“እናንተ የጢሮስ፥ የሲዶናና የፍልስጥኤም አውራጃዎች ሕዝብ ሆይ፥ ምን እያደረጋችሁ ነው? እኔን ለመበቀል ይቃጣችኋልን? ይህ ከሆነ ሥራችሁ ወዲያው በፍጥነት በራሳችሁ ላይ እንዲመለስ አደርጋለሁ።
እናንተ በባሕር ዳር የምትኖሩ ከሪታውያን ማለት ፍልስጥኤማውያን ወዮላችሁ! የእግዚአብሔር ፍርድ በእናንተ ላይ ደርሷል፤ የፍልስጥኤም ምድር ለሆንሽው ከነዓን ወዮልሽ አንድ እንኳ ነዋሪ እንዳይኖርብሽ አድርጌ አጠፋሻለሁ።
ከምናሴ ነገድ ወገን የሆነው ያኢር መላውን የአርጎብ ምድር ወረሰ፤ ይህችውም እስከ ገሹርና እስከ ማዕካ ጠረፍ የምትደርሰው ባሳን ናት፤ መንደሮቹንም በእርሱ ስም እንዲጠሩ አደረገ፤ ስለዚህ እነርሱ የያኢር መንደሮች ተብለው እስከ ዛሬ ይጠራሉ።
ግዛቱም የሔርሞንን ተራራ፥ ሳለካን፥ እስከ ገሹርና ማዕካ ድንበሮች የሚደርሰውን የባሳንን ምድር ሁሉ ጠቅልሎ፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን ይዞታ እስከሆነው ግዛት የገለዓድን እኩሌታ የሚጨምር ነበር።
በዚያን ጊዜ ውስጥ ዳዊትና ተከታዮቹ በጌሪሹራውያን፥ በጌዛውያንና በአማሌቃውያን ላይ ዘመቱ፤ እነዚህም አገሮች ከቴሌኦም ጀምሮ ወደ ሱርና ወደ ምድረ ግብጽ የሚወስዱ እነርሱ የሚኖሩባቸው አገሮች ነበሩ።