ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ኢያሱ 10:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢያሱ አምስቱን ነገሥታት ገድሎ በአምስት ዕንጨት ላይ ሰቀላቸው፤ ሬሳቸውም እስከ ምሽት ድረስ በዚያው ዋለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው፤ በዐምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው፤ ሬሳቸውም እስኪመሽ ድረስ አልወረደም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢያሱ መትቶ ገደላቸው፥ በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፤ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፤ እስከ ማታም ደረስ በዛፎቹ ላይ ተሰቅለው ቈዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፥ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፥ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ። |
ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ዳዊት እነዚህን ሁሉ ለገባዖን ሰዎች አሳልፎ ሰጠ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፤ ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ እነርሱም የተገደሉት በጸደይ ወራት ማለቂያና በገብስ መከር መጀመሪያ ላይ ነበር።
ምርመራም በተደረገ ጊዜ የቀረበው መረጃ እውነት ሆኖ ተገኘ፤ ስለዚህም ሁለቱ ዐመፀኞች በስቅላት ሞት ተቀጡ፤ ንጉሡም ይህ ሁኔታ በንጉሠ ነገሥቱ የታሪክ መዝገብ ተጽፎ እንዲቀመጥ ትእዛዝ አስተላለፈ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በእስራኤል ላይ የነደደው ቊጣዬ ይበርድ ዘንድ የእስራኤልን መሪዎች ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ በሕዝብ ፊት ግደላቸው።”
ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች፥ የተሰቀሉትን ሰዎች ጭን ሰብረው፥ አስከሬናቸውን ከመስቀል እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት የሰንበት ዝግጅት ቀን ስለ ነበረና ያ ሰንበትም ትልቅ በዓል ስለ ሆነ፥ በሰንበት ቀን ሥጋቸው በመስቀል ላይ እንዳይሆን ነበር።
“በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የሚሞት ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ ተረገመ ሰው ሆኖ ሕግ ከሚያስከትለው ርግማን ዋጀን።
የዐይንም ከተማ ንጉሥ በእንጨት ላይ ሰቅሎ ሬሳው እስከ ማታ ተንጠልጥሎ እንዲቈይ አደረገ። ፀሐይም በምትጠልቅበት ጊዜ ሬሳው ከተሰቀለበት እንጨት ላይ ወርዶ በከተማይቱ ቅጽር በር መግቢያ እንዲጣል አደረገ፤ በእርሱም ላይ ብዙ የድንጋይ ቊልል ከመሩበት፤ የድንጋዩም ቊልል እስከ አሁን በዚያው ይገኛል።
ከዚህ በኋላ ዜባሕና ጻልሙናዕ ጌዴዎንን “በል እንግዲህ አንተው ራስህ ግደለን፤ የሰው ኀይሉ እንደ ሰውነቱ ነው” አሉት፤ ስለዚህ ጌዴዎን እነርሱን ገድሎ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበረውን ጌጣጌጥ በሙሉ ወሰደ።
በዚህም ጊዜ ሳሙኤል “የአንተ ሰይፍ ብዙዎች እናቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ የአንተም እናት ልጅ አልባ ሆና ትቀራለች” አለው። ከዚህም በኋላ በጌልገላ በሚገኘው በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት አጋግን ቈራርጦ ጣለው።