ኢያሱ 1:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፤ “የነገርከንን ሁሉ እንፈጽማለን፤ ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ያዘዝኸንን ሁሉ እናደርጋለን፤ ወደምትልከንም ሁሉ እንሄዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ ሁሉ እንሄዳለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፥ “ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ለኢያሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፦ ያዘዝኸንን ነገር ሁሉ እናደርጋለን ወደምትልከንም ስፍራ እንሄዳለን። |
ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ።
ስለዚህ ወደ እርሱ ቀርበህ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ አዳምጥ፤ ተመልሰህም እርሱ ያለውን ሁሉ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እንታዘዛለን።’
እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ እንደ ሰጠው ለወንድሞቻችሁም ዕረፍትን እስኪሰጥና እነርሱም እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ርስት እስኪያገኙ አብራችሁ ዝመቱ። ከዚያ በኋላ ተመልሳችሁ መጥታችሁ፥ በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ማዶ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሰጣችሁ በገዛ ምድራችሁ ትቀመጣላችሁ።”
ለሙሴ ሁልጊዜ ስንታዘዝለት እንደ ነበረ ሁሉ፥ ለአንተም እንታዘዛለን፤ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ፥ ከአንተም ጋር ይሁን!