ዮናስ 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የዚህ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ ብናደርግ አታጥፋን፤ አንተ የፈቀድከውን ስላደረግህ ንጹሕ ደም እንዳፈሰስን አድርገህ አትቊጠርብን!” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት አታጥፋን፤ የዚህ ንጹሕ ሰው ደምም በእኛ ላይ አይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የወደድኸውን አድርገሃልና” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ወደ ጌታ ጮኹ፥ እንዲህም አሉ፦ “ጌታ ሆይ! እባክህ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ እንለምንሃለን፥ ንጹሕንም ደም በእኛ ላይ አታድርግ፤ ጌታ ሆይ ደስ የሚያሰኝህን አድርገሃልና።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደድህ አድርገሃልና ስለዚህ ሰው ነፍስ አታጥፋን፤ ንጹሕ ደምንም አታድርግብን።” አሉ። |
መርከበኞቹ ግን ባላቸው ኀይል ሁሉ እየቀዘፉ መርከቢቱን ወደ ዳር ለማድረስ ሞከሩ፤ ሆኖም ማዕበሉ እጅግ በርትቶ ስለ ነበር ይህን ማድረግ አልቻሉም።
መርከበኞቹም እጅግ ስለ ፈሩ እያንዳንዱ ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱን ክብደት ለመቀነስ አስበው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን በመርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ በመተኛቱ በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር።
የማልታ ሰዎች እባብ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው! ከባሕሩ ማዕበል በደኅና ቢወጣም ከአምላክ ፍርድ አምልጦ በሕይወት ለመኖር አልቻለም” ተባባሉ።
እግዚአብሔር ሆይ፥ ከግብጽ ምድር ዋጅተህ ያወጣሃቸውን ሕዝብህን እስራኤልን ይቅር በል፤ እኛንም ይቅር በለን፤ ስለዚህም ስለ ፈሰሰው የንጹሕ ሰው ደም በኀላፊነት ተጠያቂዎች አታድርገን።’