ዮሐንስ 8:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ፈጽሞ አይሞትም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ቃሌን ቢጠብቅ፣ ሞትን ፈጽሞ አያይም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አያይም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም። |
“ከዓለም ውስጥ መርጠህ ለሰጠኸኝ ሰዎች የአንተን ማንነት ገለጥኩላቸው፤ እነርሱ የአንተ ነበሩ፤ አንተ እነርሱን ለእኔ ሰጠኸኝ፤ እነርሱም ቃልህን ጠብቀዋል፤
“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።
አይሁድ እንዲህ አሉት፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም እንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ አይሞትም’ ትላለህ፤
ሆኖም እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ እኔ አላውቀውም ብል እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንኩ ነበር፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
ሔኖክ ሞት እንዳይደርስበት ወደ ላይ የተወሰደው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም፤ ከመወሰዱ በፊት ደግሞ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል።
አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።