Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሔኖክ ሞት እንዳይደርስበት ወደ ላይ የተወሰደው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም፤ ከመወሰዱ በፊት ደግሞ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሔኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ “እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም”፤ ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሠኘ ተመስክሮለታልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፤ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ከመወሰዱም በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሄኖክ ሞትን እን​ዳ​ያይ በእ​ም​ነት ተወ​ሰደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ወሰ​ደው አል​ተ​ገ​ኘም፤ ሳይ​ወ​ሰ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እንደ አሰ​ኘው ተመ​ስ​ክ​ሮ​ለ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 11:5
17 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የሚወስድበት ጊዜ ደረሰ፤ ኤልያስና ኤልሳዕ ከጌልጌላ ተነሥተው ጒዞ ጀመሩ፤


እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።


ሰው ሞት ሳይደርስበት እንዲሁ ለመኖር እንዴት ይችላል? ወደ መቃብር ሳይወርድ ሊቀርስ እንዴት ይችላል?


ከዚህ በኋላ ልዑሉን ይረሕምኤልን ከዐዝርኤል ልጅ ሠራያና ከዐብድኤል ልጅ ከሸሌምያ ጋር ሆኖ እኔንና ባሮክን እንዲይዝ አዘዘው፤ እኛ ግን እግዚአብሔር ሰወረን።


እርሱ የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት መንፈስ ቅዱስ ገልጦለት ነበር።


ላሜሕ የማቱሳላ ልጅ፥ ማቱሳላ የሔኖክ ልጅ፥ ሔኖክ የያሬድ ልጅ፥ ያሬድ የመላልኤል ልጅ፥ መላልኤል የቃይናን ልጅ፥


ይልቅስ እግዚአብሔር ወንጌሉን ለእኛ በዐደራ የሰጠን በእኛ ተማምኖ ስለ ሆነ እንናገራለን፤ ይህንንም የምናደርገው ልባችንን የሚመረምረውን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ብለን ነው እንጂ ሰውን ለማስደሰት ብለን አይደለም።


ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሰው እግዚአብሔር መኖሩንና እርሱን ለሚፈልጉት ሰዎችም ስጦታን የሚሰጥ መሆኑን ማመን አለበት።


አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።


የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የምንፈጽምና እርሱን ደስ የሚያሰኘውንም የምናደርግ ስለ ሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሔኖክ ሲናገር እንዲህ ብሎአል፦ “እነሆ እግዚአብሔር እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክቱ ጋር ሆኖ በሁሉም ላይ ለመፍረድ ይመጣል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos