ዮሐንስ 8:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በሥጋዊ አስተሳሰብ ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም ላይ አልፈርድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ እንደ ሰው አስተሳሰብ ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም አልፈርድም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በሥጋዊ መንገድ ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በአንድ ሰው ላይ እንኳ አልፈርድም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ ግን በማንም አልፈርድም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ሥጋዊ ፍርድን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በአንድ ሰው ስንኳ አልፈርድም። |
ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።
ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የማያውለውን የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ እኔ የመጣሁት ዓለምን ለማዳን ነው እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለም።
ኢየሱስ “የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ በአይሁድ ባለሥልጣኖች እጅ እንዳልወድቅ ሎሌዎቼ በተዋጉልኝ ነበር፤ መንግሥቴ ግን ከዚህ ዓለም አይደለችም” ሲል መለሰ።
በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።
ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም።
እግዚአብሔር ግን “የኤሊአብን ቁመት መርዘምና መልከ ቀናነቱን አትይ፤ እኔ እርሱን አልፈለግሁትም፤ እኔ የምፈርደው ሰዎች እንደሚፈርዱት አይደለም፤ ሰው የውጪ መልክን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።