ዮሐንስ 7:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ የሚያምን ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው፥ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ የሚያምን፥ መጽሐፍ እንዳለው፥ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔም የሚያምን መጽሐፍ እንደ ተናገረ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈስሳል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል” ብሎ ጮኸ። |
“ለተጠማው ምድር ውሃን እሰጣለሁ፤ በደረቀውም ምድር ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ መንፈሴን በልጆችህ ላይ አፈሳለሁ፤ በረከትንም ለልጅ ልጆችህ እሰጣለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውሃው ኑ! የምትገዙበት ገንዘብ የሌላችሁ ኑና ገዝታችሁ ብሉ! ኑና ያለ ገንዘብና ያለ ዋጋ ወተትና የወይን ጠጅን ግዙ።
እኔ ሁልጊዜ እመራችኋለሁ፤ በድርቅም ቦታ ፍላጎታችሁን አረካለሁ፤ አጥንታችሁንም አጠነክራለሁ፤ ውሃ እንደሚጠጣ የአትክልት ቦታና ደርቆ እንደማያውቅ ምንጭ ትሆናላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእነርሱ ጋር የሚኖረኝ ቃል ኪዳን ይህ ነው፦ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእናንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአንደበታችሁ ያኖርኩትን ቃሌን ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ አስተምሩ ይላል እግዚአብሔር።”
በዚያን ቀን ከኢየሩሳሌም የሕይወት ውሃ ይፈልቃል፤ ከእርሱም እኩሌታው በምሥራቅ በኩል ወደ ሙት ባሕር፥ እኩሌታው በምዕራብ በኩል ወደ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይፈስሳል፤ በበጋም ሆነ በክረምት ዓመቱን ሙሉ ሲፈስ ይኖራል።
ኢየሱስም “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ውሃ አጠጪኝ!’ የሚልሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂው ኖሮ፥ እርሱን መለመን የሚገባሽ አንቺ ነበርሽ፤ እርሱም የሕይወትን ውሃ ይሰጥሽ ነበር” አላት።
እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።”