Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 59:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእነርሱ ጋር የሚኖረኝ ቃል ኪዳን ይህ ነው፦ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእናንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአንደበታችሁ ያኖርኩትን ቃሌን ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ አስተምሩ ይላል እግዚአብሔር።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “በእኔ በኩል፣ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “በአንተም ላይ ያለው መንፈሴ፣ በአፍህ ያኖርሁት ቃሌ ከአፍህ፣ ከልጆችህ አፍ፣ ከዘር ዘሮቻቸውም አፍ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም አይለይም” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይለይም፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “በአ​ንተ ላይ ያለው መን​ፈሴ በአ​ፍ​ህም ውስጥ ያደ​ረ​ግ​ሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ ከአ​ፍህ፥ ከዘ​ር​ህም አፍ፥ ከዘር ዘር​ህም አፍ አይ​ጠ​ፋም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል እግዚአብሔር፥ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ ከአፍህ ከዘርህም አፍ ከዘር ዘርህም አፍ አያልፍም፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 59:21
36 Referencias Cruzadas  

ተስፋ የማደርገው የአንተን ፍርድ ስለ ሆነ ዘወትር እውነት እንድናገር እርዳኝ።


ለእርሱ ትነግረዋለህ፤ የሚናገረውንም ቃል ታስረዳዋለህ፤ ሁለታችሁም እንዴት መናገር እንደምትችሉና ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ አስተምራችኋለሁ፤


እንደ ጣትህ ቀለበት ጠብቃቸው፤ በልብህም ሰሌዳ ቅረጻቸው።


ነገር ግን እግዚአብሔር መንፈሱን በእኛ ላይ የሚያፈስበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ምድረ በዳው ለም ይሆናል፤ ለሙም መሬት ብዙ ፍሬ ይሰጣል።


በእርግጥ ሣር ይደርቃል፤ አበባም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።


“ለተጠማው ምድር ውሃን እሰጣለሁ፤ በደረቀውም ምድር ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤ መንፈሴን በልጆችህ ላይ አፈሳለሁ፤ በረከትንም ለልጅ ልጆችህ እሰጣለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ።


ቃሌን በአንደበትሽ አሳድራለሁ፤ አንቺንም በእጄ ጥላ ሥር እጋርድሻለሁ፤ ሰማያትን የዘረጋሁ፥ ምድርንም የመሠረትኩ እኔ ነኝ፤ ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ እላታለሁ።”


ተራራዎችና ኰረብቶች ሊናወጡና ሊፈርሱ ይችላሉ፤ እኔ ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ የሰላምንም የተስፋ ቃሌን ለዘለዓለም እጠብቅልሻለሁ፤” ይላል ለአንቺ የሚራራ እግዚአብሔር።


ከእኔ አንደበት የሚወጣውም ቃል እንደዚሁ ነው። እርሱ የላክሁትን ጉዳይ ሳያከናውንና ተልእኮውን ሳይፈጽም ወደ እኔ አይመለስም።


“ጆሮአችሁን አዘንብላችሁ ወደ እኔ ቅረቡ፤ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ቃሌን አድምጡ፤ ዳዊትን እንደ ወደድኩት እናንተን በታማኝነት ለመውደድ ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።


በሩቅና በቅርብ ላሉትም ሁሉ ሰላም ይሁን! እኔ ሕዝቤን እፈውሳለሁ፤


“የምፈጥራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በእኔ ጸንተው እንደሚኖሩ እንዲሁም ዘራችሁና ስማችሁ በእኔ ጸንተው ይኖራሉ፤


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እጁን ዘርግቶ ከንፈሮቼን ዳሰሰ፤ እንዲህም አለኝ፦ “እነሆ የምትናገረውን ቃሌን ሰጥቼሃለሁ፤


እኔ ራሴ አላውቀውም ነበር፤ ነገር ግን በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝ፥ ‘መንፈስ ቅዱስ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍበት የምታየው በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቅ እርሱ ነው’ ሲል ነግሮኛል።


የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤ እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ ዘንድ መጥቼ መምጣቴንም በእውነት ዐውቀዋል፤ አንተ እንደ ላክኸኝም አምነዋል።


እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጠው መጥኖ ስላልሆነ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል።


እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘለዓለም ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ፥ ለሚጠጣው ሰው ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል።”


ይህንንም የተናገረው በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት ስለ መንፈስ ቅዱስ ነበር፤ ኢየሱስ ገና ወደ ክብር ስላልወጣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር።


እኔ ከአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተ ግን ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”


ኃጢአታቸውንም በደመሰስኩላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው።”


እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ የሚኖር ከሆነ በመንፈስ ፈቃድ እንጂ በሥጋ ፈቃድ አትኖሩም፤ የክርስቶስ መንፈስ የሌለውም ሰው የክርስቶስ ወገን አይደለም።


ታዲያ፥ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚገኘው አገልግሎት የበለጠ ክብር አይኖረውምን?


“ከእነዚያ ቀኖች በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በአእምሮአቸውም እጽፈዋለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos