ዮሐንስ 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በሽተኞችን በመፈወስ ያደረገውን ተአምር ስላዩ ተከተሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሰዎችም በሽተኞችን በመፈወስ ያደረጋቸውን ታምራዊ ምልክቶች ስላዩ ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበሽተኞችም ላይ ያደረገውን ተአምራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። |
ይሁን እንጂ ሰውየው ከዚያ ወጥቶ ይህን ነገር ለሰው ሁሉ ማውራት ጀመረ። በዚህም ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማናቸውም ከተማ በግልጥ መግባት አልቻለም። ነገር ግን ከከተማ ውጪ ሰው በሌለበት ቦታ ይኖር ነበር፤ ሆኖም ሰዎች ከየስፍራው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሸንጎውን አባሎች ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ስለሚያደርግ ምን ብናደርግ ይሻላል?
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በቀር እነዚህን አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል ማንም የለም፤ ስለዚህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንክ እናውቃለን” አለው።
በማግስቱ ከባሕሩ ማዶ ቀርተው የነበሩት ሰዎች፥ በባሕሩ ላይ አንድ ጀልባ ብቻ እንደ ነበረና በዚያም ደቀ መዛሙርቱ ብቻቸውን እንደ ሄዱ፥ ኢየሱስ ግን ከእነርሱ ጋር ወደ ጀልባዋ እንዳልገባ አይተው ነበር።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ተአምራት ስላያችሁ አይደለም።