Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 6:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “እኛ አይተን በአንተ እንድናምን ምን ተአምር ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ስለዚህ እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ “አይተን እንድናምንህ ምን ታምራዊ ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እንዲህም አሉት፦ “ታዲያ አይተን እንድናምንህ አንተ ምን ዓይነት ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “የም​ት​ሠ​ራ​ውን አይ​ተን በአ​ንተ እና​ምን ዘንድ ምን ተአ​ም​ራት ታደ​ር​ጋ​ለህ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እንግዲህ፦ እንኪያ አይተን እንድናምንህ አንተ ምን ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 6:30
22 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ይህን ምልክት ይሰጣል፤ ይህ መሠዊያ ተሰባብሮ ይወድቃል፤ በእርሱ ላይ ያለውም ዐመድ ይበተናል፤ ይህንንም የትንቢት ቃል በእኔ አማካይነት የተናገረው ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ይህ እንደ ተፈጸመ ወዲያውኑ ትገነዘባለህ’ ” አለ።


የእግዚአብሔርም ነቢይ በእግዚአብሔር ስም በተናገረው የትንቢት ቃል መሠረት በእግዚአብሔር የተሰጠውም ምልክት ተፈጸመ፤ መሠዊያው ወዲያውኑ ተሰባብሮ ወደቀ፤ ዐመዱም መሬት ላይ ፈሰሰ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ በመጀመሪያው ተአምር ባያምኑና እውነት ነው ብለው ባይቀበሉህ፥ ሁለተኛውን ተአምር ያምናሉ።


“ፈርዖን ‘እስቲ ተአምራት በማድረግ ማንነታችሁን ግለጡልኝ’ ቢላችሁ ለአሮን ንገረውና በትሩን ወስዶ በንጉሡ ፊት ይጣለው፤ በዚያን ጊዜ በትሩ ተለውጦ እባብ ይሆናል።”


“እኛ በዐይናችን እናያት ዘንድ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያቀደውን በፍጥነት ያድርግ፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ያቀዳት ምክር ትፈጸም” ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው!


እርሱ መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እንይና እንመንበት!” እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎች ይሰድቡት ነበር።


ፈሪሳውያን ወደ ኢየሱስ መጡና ከእርሱ ጋር መከራከር ጀመሩ፤ ሊፈትኑትም አስበው ከሰማይ አንድ ተአምር እንዲያሳያቸው ጠየቁት።


የአባቴን ሥራ የምሠራ ከሆንኩ ግን በእኔ እንኳ ባታምኑ በሥራዬ እመኑ፤ በዚህ ዐይነት አብ በእኔ እንደ ሆነና እኔም በአብ እንደ ሆንኩ በሚገባ ታውቃላችሁ።”


ኢየሱስም ብዙ ተአምራትን በፊታቸው ቢያደርግም እንኳ አይሁድ በእርሱ አላመኑም።


ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን፦ “አንተ ይህን ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ ምን ተአምር ታሳየናለህ?” አሉት።


በዚያን ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበር።


ሰዎቹም ኢየሱስ ያደረገውን ተአምር ባዩ ጊዜ፥ “በእርግጥ ይህ ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው!” አሉ።


ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በሽተኞችን በመፈወስ ያደረገውን ተአምር ስላዩ ተከተሉት።


እናንተ ግን አይታችሁኛል፤ ግን በእኔ አላመናችሁም እላችኋለሁ።


በቅዱሱ ልጅህ በኢየሱስ ስም በሽተኞች እንዲድኑና ተአምራትም፥ ድንቅ ነገሮችም እንዲደረጉ እጅህን ዘርጋ።”


መቼም አይሁድ ተአምር ማየትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎች ደግሞ ጥበብን ይሻሉ።


እግዚአብሔርም ደግሞ ምልክቶችን፥ ድንቅ ነገሮችን፥ ልዩ ልዩ ተአምራትን በማድረግና እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቸውን አጽንቶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos