እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በተቀደሰው ቀኔ የራሳችሁን ጥቅም በማሳደድ ሰንበቴን ከመሻር ብትቈጠቡ፥ ሰንበቴን አስደሳች፥ የተከበረውንም የእኔን የእግዚአብሔርን ቀን የተከበረ ቀን ብትሉት፥ የግል ፍላጎታችሁንና የግል ጉዳያችሁን ተግባራዊ ለማድረግ በራሳችሁ አካሄድ መመራትን ትታችሁ ሰንበቴን ብታከብሩ፥
ዮሐንስ 5:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ያንን የዳነውን ሰው “ዛሬ ሰንበት ስለ ሆነ አልጋህን እንድትሸከም ሕግ አይፈቅድልህም” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም የተፈወሰውን ሰው፣ “ሰንበት ስለ ሆነ መተኛህን እንድትሸከም ሕጉ አይፈቅድልህም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው “ሰንበት ነው፥ አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም፤” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም የዳነውን ሰው፥ “ዛሬ ሰንበት ነው፤ አልጋህን ልትሸከም አይገባህም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው፦ ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በተቀደሰው ቀኔ የራሳችሁን ጥቅም በማሳደድ ሰንበቴን ከመሻር ብትቈጠቡ፥ ሰንበቴን አስደሳች፥ የተከበረውንም የእኔን የእግዚአብሔርን ቀን የተከበረ ቀን ብትሉት፥ የግል ፍላጎታችሁንና የግል ጉዳያችሁን ተግባራዊ ለማድረግ በራሳችሁ አካሄድ መመራትን ትታችሁ ሰንበቴን ብታከብሩ፥
ሕይወታችሁን ለማዳን እኔ የምሰጣችሁን ማስጠንቀቂያ ጠብቁ፤ ስለዚህ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች አትግቡ።
ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”
በዚያም አንድ እጀ ሽባ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስን የሚከሱበትን ምክንያት የፈለጉ አንዳንድ ሰዎች “በሰንበት ቀን በሽተኛን መፈወስ ተፈቅዶአልን?” ሲሉ ጠየቁት።
ከዚያም በኋላ “ለመሆኑ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ።
ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ የምኲራቡ አለቃ ተቈጣና ለሕዝቡ፦ “በሳምንት ውስጥ ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ በእነዚህ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም” ብሎ ተናገረ።
የአይሁድ ባለሥልጣኖች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ወደ ዮሐንስ ልከው፦ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ባስጠየቁት ጊዜ የሰጠው ምስክርነት የሚከተለው ነው፤
እንግዲህ በሙሴ አማካይነት የተሰጠው ሕግ እንዳይሻር በሰንበት ቀን ሰው የሚገረዝ ከሆነ ታዲያ፥ እኔ በሰንበት ቀን የሰውን ሁለንተና በመፈወሴ ስለምን ትቈጣላችሁ?
በዚህ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፥ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን “ታዲያ፥ ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እነዚህን ተአምራት እንዴት ማድረግ ይችላል?” አሉ። በዚህ ምክንያት በመካከላቸው መለያየት ሆነ።