በዚያን ጊዜ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “የገሊላ ሰዎች መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ ጲላጦስ ገደላቸው፤ ደማቸውም ከመሥዋዕታቸው ጋር አደባለቀ” ሲሉ ነገሩት።
ዮሐንስ 4:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወደ ገሊላ በደረሰ ጊዜ የገሊላ ሰዎች በመልካም ሁኔታ ተቀበሉት፤ ይህም የሆነው ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ሄደው በነበረበት ጊዜ እርሱ በዚያ ያደረገውን ሁሉ አይተው ስለ ነበር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገሊላ እንደ ደረሰም የገሊላ ሰዎች በደስታ ተቀበሉት፤ ምክንያቱም፣ እነርሱም በፋሲካ በዓል ኢየሩሳሌም ስለ ነበሩና በዚያ ያደረገውን ሁሉ ስላዩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ገሊላም በመጣ ጊዜ፥ የገሊላ ሰዎች፥ እራሳቸውም ለበዓል መጥተው ነበርና፥ በበዓል በኢየሩሳሌም ያደረገውን ሁሉ ስላዩ ተቀበሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ገሊላም ደግሞ በገባ ጊዜ ገሊላውያን ሁሉ ተቀበሉት፤ እነርሱ ለበዓል ሄደው ስለ ነበር በበዓሉ ቀን በኢየሩሳሌም ያደረገውን ተአምር አይተው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ገሊላም በመጣ ጊዜ፥ የገሊላ ሰዎች ራሳቸው ደግሞ ለበዓል መጥተው ነበርና በበዓል በኢየሩሳሌም ያደረገውን ሁሉ ስላዩ ተቀበሉት። |
በዚያን ጊዜ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፥ “የገሊላ ሰዎች መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ ጲላጦስ ገደላቸው፤ ደማቸውም ከመሥዋዕታቸው ጋር አደባለቀ” ሲሉ ነገሩት።
ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ “መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በቀር እነዚህን አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል ማንም የለም፤ ስለዚህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር እንደ ሆንክ እናውቃለን” አለው።
“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ የፋሲካን፥ የመከርንና የዳስ በዓልን ለማክበር እግዚአብሔር አምላክህ በሚመርጠው ቦታ ይሰብሰቡ፤ በዓሉን ለማክበር በሚወጡበት ጊዜ ባዶ እጃቸውን አይምጡ፤