አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
ዮሐንስ 4:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ፥ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ እንዲያውም አሁን መጥቶአል፤ አብም የሚፈልገው በዚህ መንገድ የሚሰግዱለትን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ አሁንም መጥቷል፤ አብም እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ይፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ ይኸውም አሁን ነው፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ በመንፈስና በእውነት ለአብ የሚሰግዱባት ጊዜ ትመጣለች፤ እርስዋም አሁን ናት። አብ እንዲህ የሚሰግዱለትን ይሻልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ |
አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
እግዚአብሔር ሆይ! ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት የማቀርብልህን ጸሎት ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በሽንገላ ሳይሆን በእውነት የማቀርበውን ጸሎት ስማ።
አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤ እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ ድምፅሽ አስደሳች ነው፤ ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።
በዚያን ጊዜ ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ፥ ጥቃት ባደረሱባቸው በአሦራውያን ላይ አይተማመኑም፤ በዚህ ፈንታ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይተማመናሉ።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው።
ሆኖም ዕለት በዕለት ይሹኛል፤ መንገዶቼንም ማወቅ ደስ ይላቸዋል፤ ጽድቅን እንደሚያዘወትሩና የእኔን የአምላካቸውን ትእዛዝ እንዳልተወ ሕዝብ ከእኔ ትክክለኛውን ፍርድ ይለምናሉ፤ ወደ እኔ ወደ አምላክም በመቅረብ ይደሰታሉ።”
ይህን ሁሉ ከፈጸመች በኋላ እምነት የማይጣልባት የእስራኤል እኅት የሆነችው ይሁዳ፥ እንደገና ወደ እኔ ለመመለስ የምትሞክር መስላ የታየችው ከልብዋ ሳይሆን ከአንገት በላይ ነበር፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
በቊጣዬ አገሪቱን ከማጥፋቴ በፊት የቅጽር ግንብ የሚሠራ፥ ቅጽሮቹ በፈረሱበት በኩል በመቆም በእኔና በሕዝቡ መካከል ገብቶ ቊጣዬን የሚያበርድ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንንም አላገኘሁም።
ይሁን እንጂ እያንዳንዳችሁ በየበኩላችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ ሰዓቱም አሁን ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የሞቱ ሰዎች የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ ጊዜውም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም ሁሉ በሕይወት ይኖራሉ።
ስለዚህ “አባ! አባታችን ሆይ!” ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ በፍርሃት ለመኖር እንደገና የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም።
እኛ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናመልክና በውጭ በሚታየው ሥርዓት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የምንመካ ስለ ሆንን በእውነት ተገርዘናል።
ኢያሱ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ እግዚአብሔርን አክብሩት፤ በፍጹም ቅንነትና በታማኝነት አገልግሉት፤ የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶና በግብጽ ይሰግዱላቸው የነበሩትን ባዕዳን አማልክት አስወግዳችሁ እግዚአብሔርን ብቻ አምልኩ፤
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።