ዮሐንስ 21:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ለማጥመድ መሄዴ ነው” አላቸው። እነርሱም “ከአንተ ጋር እንሄዳለን” አሉት፤ ወጥተውም ሄዱና ወደ ጀልባ ገቡ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት አንድ ዓሣ እንኳ አልያዙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምዖን ጴጥሮስም፣ “ዓሣ ላጠምድ መሄዴ ነው” አላቸው፤ እነርሱም፣ “እኛም ከአንተ ጋራ እንሄዳለን” አሉት። ወጥተውም ወደ ጀልባዋ ገቡ፤ በዚያ ሌሊት ግን ምንም አላጠመዱም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። እነርሱም “እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን” አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም አላጠመዱም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምዖን ጴጥሮስ፥ “እኔ ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው፤ እነርሱም፥ “እኛም አብረንህ እንመጣለን” አሉት፤ ሄደውም ወደ ታንኳ ገቡ፤ ግን በዚያች ሌሊት የያዙት ምንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምዖን ጴጥሮስ፦ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። እነርሱም፦ “እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን” አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ በዚያችም ሌሊት ምንም እላጠመዱም። |
ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።