ዮሐንስ 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሦስተኛው ቀን፥ በገሊላ ምድር በምትገኘው ቃና በምትባል ከተማ ሠርግ ነበረ፤ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሦስተኛው ቀን፣ በገሊላ አውራጃ፣ በቃና ከተማ ሰርግ ነበር፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሦስተኛውም ቀን የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና ሰርግ ሆነ፤ የጌታችን የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤ |
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ ወደ ለወጠባት በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ እንደገና ተመለሰ፤ በዚያን ጊዜ በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት አንድ የቤተ መንግሥት ሹም ነበረ።
ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።