ዮሐንስ 18:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ እዚያ ቦታ ዘወትር ይሰበሰቡ ስለ ነበር አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ያን ቦታ ያውቅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙውን ጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ በዚያ ስለሚገናኝ፣ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ቦታውን ያውቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ብዙ ጊዜ ወደዚያ ስለ ተሰበሰቡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ስፍራውን ያውቅ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ያን ስፍራ ያውቀው ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደዚያ ብዙ ጊዜ ይሄድ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ጊዜ ወደዚያ ስለ ተሰበሰቡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ደግሞ ስፍራውን ያውቅ ነበር። |