ዮሐንስ 16:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማያስፈልግህ አሁን ዐወቅን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ወጣህ እናምናለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ሁሉን ነገር እንደምታውቅና ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ ተረድተናል፤ ይህም ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እንድናምን አድርጎናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ፥ እንዲሁም ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናምናለን፤” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን አንተ ሁሉን እንደምታውቅ፥ ማንም ሊነግርህ እንደማትሻ ዐወቅን፤ በዚህም ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን” አሉት። |
ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶች፥ “ይህ፥ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ደግሞ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ፤ ደግሞ ወደ አብ እሄዳለሁ’ የሚለን ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ።
የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ፤ እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ ዘንድ መጥቼ መምጣቴንም በእውነት ዐውቀዋል፤ አንተ እንደ ላክኸኝም አምነዋል።
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆንማ እኔን በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የላከኝ እርሱ ነው እንጂ እኔ በራሴ ሥልጣን አልመጣሁም።
ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ በእርሱ ዐይን ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው፤ እኛም መልስ መስጠት የሚገባን በእርሱ ፊት ነው።