ዮሐንስ 12:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የማያውለውን የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ እኔ የመጣሁት ዓለምን ለማዳን ነው እንጂ በዓለም ላይ ለመፍረድ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ቃሌን ሰምቶ በማይፈጽመው ላይ የምፈርደው እኔ አይደለሁም፤ ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ላይ ልፈርድ አልመጣሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና፤ ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀውን እኔ የምፈርድበት አይደለሁም፤ ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድበት አልመጣሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም። |
ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ ነገር አለኝ፤ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ለዓለም የምናገረው ከእርሱ የሰማሁትን ነው።”