የሰሜን ነፋስ ሆይ! ንቃ! አንተም የደቡብ ነፋስ ሆይ! ወደዚህ ና! በአትክልት ቦታዬም ላይ ንፈስ፤ ዐየሩም በመልካም ሽታ የተሞላ ይሁን፤ ውዴም ወደ አትክልት ቦታው ይምጣ፤ ምርጥ የሆኑትንም ፍሬዎች ይመገብ።
ዮሐንስ 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ራት አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግል ነበር፤ አልዓዛርም ከኢየሱስ ጋር በማእድ ቀርበው ከነበሩት አንዱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ለኢየሱስ ሲባል እራት ተዘጋጀ። ማርታ ስታገለግል፣ አልዓዛር ከርሱ ጋራ በማእድ ከተቀመጡት አንዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም እራት አዘጋጁለት፤ ማርታም ታገለግል ነበር፤ አልዓዛር ግን ከእርሱ ጋር ከተቀመጡት መካከል አንዱ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ምሳ አደረጉለት፤ ማርታም ታሳልፍላቸው ነበር፤ አብረውት ምሳ ከበሉትም አንዱ አልዓዛር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም እራት አደረጉለት፤ ማርታም ታገለግል ነበር፤ አልዓዛር ግን ከእርሱ ጋር ከተቀመጡት አንዱ ነበረ። |
የሰሜን ነፋስ ሆይ! ንቃ! አንተም የደቡብ ነፋስ ሆይ! ወደዚህ ና! በአትክልት ቦታዬም ላይ ንፈስ፤ ዐየሩም በመልካም ሽታ የተሞላ ይሁን፤ ውዴም ወደ አትክልት ቦታው ይምጣ፤ ምርጥ የሆኑትንም ፍሬዎች ይመገብ።
ኢየሱስ በቢታንያ ለምጻም በነበረው በስምዖን ቤት ነበር። በገበታም ቀርቦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነና የከበረ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት፥ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡን ሰብራ ሽቶውን በኢየሱስ ራስ ላይ አፈሰሰችው።
እነዚያ ጌታቸው ድንገት በመጣ ጊዜ፥ ነቅተው ሲጠብቁ የሚያገኛቸው አገልጋዮች እንዴት የተመሰገኑ ናቸው? በእውነት እላችኋለሁ፤ እርሱ ባጭር ታጥቆ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
ኢየሱስ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፦ “የምሳ ወይም የእራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ብድራቸውን ለመመለስ በተራቸው የሚጋብዙህን ወዳጆችህን፥ ወንድሞችህን፥ ዘመዶችህን፥ ሀብታሞች ጐረቤቶችህንም አትጥራ፤
በማእድ ተቀምጦ ከሚመገበውና ቆሞ ከሚያገለግለው የትኛው ነው ትልቅ? ትልቅ የሚባለው በማእድ የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በመካከላችሁ እንደ አገልጋይ ነኝ።
እነሆ! እኔ በበር ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ ገብቼ ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፤