እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው።
ዮሐንስ 1:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አገኘውና “ተከተለኝ!” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም፣ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አግኝቶ፣ “ተከተለኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ፈለገ፤ ፊልጶስንም አገኘውና “ተከተለኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ወሰደው፤ ጌታችን ኢየሱስም ባየው ጊዜ፥ “ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህን? አንተ ኬፋ ትባላለህ፤” አለው፤ ትርጓሜውም ጴጥሮስ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ፦ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ጴጥሮስ ማለት ነው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔን ላልጠየቁኝ ተገለጥኩላቸው፤ ላልፈለጉኝም ተገኘሁላቸው፤ ስሜንም ላልጠራ ሕዝብ ‘እነሆ፥ እዚህ አለሁ፥ እነሆ፥ እዚህ አለሁ’ አልኳቸው።
ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ተነሥቶ ሲሄድ ሳለ ማቴዎስ የተባለውን ቀራጭ በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ!” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ተከተለው።
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ ቀና ብሎ አየና ፊልጶስን፦ “ለዚህ ሁሉ ሰው የሚበቃ ምግብ ከየት መግዛት እንችላለን?” አለው።
ይህን ሁሉ ገና አላገኘሁም፤ ወይም በዚህ ሁሉ ፍጹም ሆኜአለሁ ለማለት አልችልም፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔን የእርሱ አድርጎ ያዘጋጀልኝን ሽልማት ለማግኘት ወደፊት በመሮጥ እተጋለሁ።