ዮሐንስ 1:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ የጸጋ ሙላት እኛ ሁላችን በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀብለናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀብለናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ሁላችንም ከሙላቱ ተቀበልን፥ በጸጋ ላይ ጸጋን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም ሁላችን ከሙላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀበልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ |
እንደ ተራራ በፊትህ የተደቀነው መሰናክል ሁሉ ይወገዳል፤ ቤተ መቅደሱንም መልሰህ ትሠራለህ፤ የመደምደሚያውንም ድንጋይ በስፍራው መልሰህ በምታኖርበት ጊዜ ሕዝቡ ‘እንዴት ውብ ነው! ውብ ነው!’ እያሉ የደስታ ድምፅ ያሰማሉ።”
እነሆ፥ እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ እርሱ ከእኔ እጅግ ይበልጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ እንኳ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም።
በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት ሞት በሰው ሁሉ ላይ ሥልጣን ካገኘ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና ነጻ ስጦታ ተቀብለው የጸደቁ ሁሉ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በድል አድራጊነት በሕይወት ይኖራሉ።
ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።
እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ የሚኖር ከሆነ በመንፈስ ፈቃድ እንጂ በሥጋ ፈቃድ አትኖሩም፤ የክርስቶስ መንፈስ የሌለውም ሰው የክርስቶስ ወገን አይደለም።
ከእነርሱ ውስጥ የነበረውም የክርስቶስ መንፈስ በመሲሑ ላይ ስለሚደርሰው መከራና ከመከራውም በኋላ ስለሚያገኘው ክብር አስቀድሞ አመልክቶ ነበር፤ እነርሱም ይህ ሁሉ በምን ጊዜና በእንዴት ያለ ሁኔታ እንደሚሆን መርምረው ነበር፤
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ በዐቀደው መሠረት ለተመረጣችሁት፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመታዘዝና በደሙ ተረጭታችሁ ለመንጻት በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሳችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።