አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
ኢዮብ 22:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአንተ መልካም ሥራ ሁሉን ለሚችል አምላክ ምን ይጠቅመዋል? የኑሮህስ ፍጹምነት ለእርሱ ምን ይረባዋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን ቻዩን አምላክ ምን ደስ ታሠኘዋለህ? መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ በሥራህ ንጹሕ ከሆንህ እግዚአብሔርን ምን ያገደዋል? መንገድህንስ ብታቀና ምን ይጠቅመዋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን? |
አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ፈትነህ፥ ታማኝ በሆነ ሕዝብ እንደምትደሰት ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም እኔ ይህን ሁሉ በፈቃዴ ለአንተ የሰጠሁት፥ በታማኝነትና በቅንነት ነው፤ ደግሞም እዚህ የተሰበሰበው ሕዝብህ ለአንተ ስጦታ በማቅረቡ፥ እጅግ መደሰቱን ተገንዝቤአለሁ፤
በቃላችሁ እግዚአብሔርን አሰልችታችሁታል፤ “እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው?” ትላላችሁ፤ እርሱን ያሰለቻችሁት፦ “ክፉ አድራጊ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፤ እግዚአብሔርንም ያስደስተዋል” በማለት ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” ብላችሁ በመጠየቅ ነው።
እንግዲህ ወዳጆቼ ሆይ፥ ይህ ሁሉ ተስፋ የተሰጠው ለእኛ ስለ ሆነ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችን ፍጹም እንዲሆን እናድርግ።
የሚያስፈልገኝንና ከሚያስፈልገኝም በላይ የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ፤ ይህም የእናንተ ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአብሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው።