ኢዮብ 22:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን ቻዩን አምላክ ምን ደስ ታሠኘዋለህ? መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 የአንተ መልካም ሥራ ሁሉን ለሚችል አምላክ ምን ይጠቅመዋል? የኑሮህስ ፍጹምነት ለእርሱ ምን ይረባዋል? Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 አንተ በሥራህ ንጹሕ ከሆንህ እግዚአብሔርን ምን ያገደዋል? መንገድህንስ ብታቀና ምን ይጠቅመዋል? Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን? Ver Capítulo |
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።