የአቤሴሎምን ያኽል በመልከ መልካምነቱ የታወቀ ሰው በእስራኤል ምድር ከቶ አልነበረም፤ አቤሴሎም ከራስ ጠጒሩ እስከ እግር ጥፍሩ ምንም እንከን የሌለበት ሰው ነበር፤
ኢዮብ 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ኢዮብን ከራስ ጠጒሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ በከባድ ቊስል እንዲሠቃይ አደረገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ኢዮብንም ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጕሩ በክፉ ቍስል መታው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይጣንም ከጌታ ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ መርገጫ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቁስል መታው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው። |
የአቤሴሎምን ያኽል በመልከ መልካምነቱ የታወቀ ሰው በእስራኤል ምድር ከቶ አልነበረም፤ አቤሴሎም ከራስ ጠጒሩ እስከ እግር ጥፍሩ ምንም እንከን የሌለበት ሰው ነበር፤
እግዚአብሔርም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው። መንፈሱም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው።’ ”
ከዚህም የተነሣ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ጠጒር ድረስ ጤናማ የሆነ የአካል ክፍል የላችሁም፤ ቊስልና እባጭ መግልም የሞላበት ሆኖአል፤ ይህም ቊስላችሁ አልፈረጠም፤ አልታሰረም፤ ወይም በዘይት አለሰለሰም።
እግዚአብሔር ቅልጥምህንና ጭንህን በማይፈወስ ቊስል እንዲሸፈን ያደርጋል፤ ብርቱ ቊስልና እባጭ ከራስ ጠጒርህ እስከ እግር ጥፍርህ ይሸፍንሃል።