ጸሎታቸውን ስማ፤ በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብን የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
ኤርምያስ 8:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ተናገር አለኝ፦ “የወደቀ ሰው እንደገና መነሣት አይችልምን? መንገድ ተሳስቶት የጠፋ ሰው አይመለስምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲህ በላቸው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሰዎች ቢውድቁ፣ እንደ ገና ከወደቁበት አይነሡምን? ሰው ተሳስቶ ወደ ኋላ ቢሄድ፣ ከስሕተቱ አይመለስምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ትላቸዋለህ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የወደቀ አይነሣምን? የሳተስ አይመለስምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ትላቸዋለሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን? |
ጸሎታቸውን ስማ፤ በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብን የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥
ክፉዎች አካሄዳቸውን፥ ኃጢአተኞች ክፉ ሐሳባቸውን ይተዉ፤ ምሕረቱ ብዙ ስለ ሆነ ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ።
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚገኙ ነቢያትም ከዚህ የባሰ ክፋት ሲያደርጉ አይቼአለሁ፤ እነርሱ ያመነዝራሉ፤ ሐሰትም ይናገራሉ፤ ሰዎችን ለክፉ ሥራ ያነሣሣሉ፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ ከክፉ ሥራቸው አይመለሱም። ስለዚህ እነርሱ በእኔ ዘንድ እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ሕዝብ የከፉ ናቸው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ እርስዋም ከእርሱ ተለይታ ሌላ ወንድ ካገባች በኋላ እንደገና መልሶ ሊያገባት ይችላልን? ይህ ቢደረግማ ፈጽሞ ምድርን የሚያረክስ ይሆናል። እስራኤል ሆይ! አንቺ ግን ብዙ ጣዖቶችን ወደሽ ነበር፤ አሁን ደግሞ እንደገና ወደ እኔ መመለስ ትፈልጊያለሽ።
እናንተ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ እርሱ ይፈውሳችኋል፤ ታማኞችም ያደርጋችኋል። እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ “አዎ! እግዚአብሔር አምላካችን ስለ ሆነ ወደ እርሱ እንመለሳለን፤
የይሁዳ ሕዝብ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት በሚሰሙበት ጊዜ ምናልባት ከክፉ ሥራቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደ እኔ ለመመለስ ከፈለጋችሁ እነዚያን አጸያፊ ጣዖቶችን አስወግዳችሁ ለእኔ ብቻ ታማኞች ብትሆኑ፥
እኔ በክፉ ሰው ሞት የምደሰት ይመስላችኋልን? አይደለም፤ እኔ ደስ የሚለኝ ስለ ኃጢአቱ ንስሓ ገብቶ በሕይወት በሚኖር ሰው ነው፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።