ኤርምያስ 8:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ተጠንቀቁ! እነሆ የአስማተኛ ድግምት ሊገታቸው የማይችል መርዘኛ እባቦችንና እፉኝቶችን በመካከላችሁ እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣ የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ይነድፏችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ መርዛቸውን አስማት የማያረክሰው እባቦችንና እፉኝቶችን በእናንተ መካከል እልካለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ አስማት የማይከለክላቸውን የሚገድሉ እባቦችን እሰድድባችኋለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ፥ እነርሱም ይነድፉአችኋል። |
የፍልስጥኤም ሕዝብ ሆይ! እነሆ የተደበደባችሁበት በትር ተሰበረ፤ ሆኖም ደስ ሊላችሁ አይገባም፤ አንድ እባብ በሞተ ጊዜ ሌላ ከእርሱ የባሰ በቦታው ይተካል፤ ከእባብ ዕንቊላል በክንፍ የሚበር እሳት የመሰለ ዘንዶ ይፈለፈላል።
ያ ቀን አንድ ሰው ከአንበሳ ሸሽቶ ሲሄድ ድብ እንደሚያጋጥመው፥ ወይም አምልጦ ወደ ቤቱ ሲገባ እጁን በግድግዳ ላይ ቢያሳርፍ እባብ እንደሚነድፈው ሁኔታ ይሆንባችኋል።
በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ወጥተው ቢሸሸጉም ተከታትዬ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ ወደ ጥልቅ ባሕር ገብተው ከእኔ ለመሰወር ቢሞክሩም እንዲነድፋቸው የባሕሩን ዘንዶ አዛለሁ።