ኤርምያስ 6:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውብና አስደሳች የሆነችው የጽዮን ከተማ ትጠፋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውብና ሽሙንሙን የሆነችዋን፣ የጽዮንን ሴት ልጅ አጠፋታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተዋበችውንና የተቀማጠለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሳቁላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅምጥል የጽዮን ልጅ ሆይ! ውበትሽ ይጐሳቈላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተዋበችውንና የተሰባቀለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሰቍላለሁ። |
ምጥ የያዛት ሴት የምታሰማውን ጩኸት የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፤ የመጀመሪያ ልጅዋን የምትወልድ በካር ሴት የምታሰማውን ድምፅ የመሰለ ኡኡታም አዳመጥኩ፤ ይህም ድምፅ ኢየሩሳሌም ትንፋሽ አጥሮአት እጅዋን ዘርግታ “ወዮልኝ! ጠፋሁ! እነሆ ሊገድሉኝ መጡ!” እያለች የምታሰማው ጩኸት ነበር።
እግዚአብሔር በቊጣው ጽዮንን ምንኛ አዋረዳት! ወደ ሰማይ ከፍ ብላ የነበረችውን የእስራኤልን መመኪያ ወደ ምድር ጣላት፤ በቊጣው ቀን የእግሩ ማሳረፊያ መሆንዋን ሊያስታውስ አልፈቀደም።
ምን ልበላችሁ? ከምንስ ጋር ላነጻጽራችሁ? የተወደደችው ከተማ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! እንዳጽናናችሁ ከምን ጋር ላመሳስላችሁ? በተለይ የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ ሆይ! የሚደርስባችሁ ጥፋት እንደ ባሕር መጠኑ ሰፊ ስለ ሆነ፥ ማን ሊፈውሳችሁ ይችላል?
ቀደም ብለው ምርጥ ምግብ ይመገቡ የነበሩት፥ አሁን በመንገድ ላይ ወድቀዋል። ሐምራዊ ልብስ ለብሰው ያደጉት አሁን በዐመድ ክምር ላይ ተጋደሙ።
በመለሳለስና በቅምጥልነት በመካከልህ የምትኖር በትውልድዋ የምትመካና ከመለስለስዋ ብዛት እግሮችዋ መሬት ረግጠው የማያውቁ ዐቅፋው ከምትተኛው ባልዋና ከልጆችዋ ትሰስታለች።