ኤርምያስ 51:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮችዋ በከተሞቻቸው መንገዶች ላይ ቈስለው ይሞታሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባቢሎን ምድር ታርደው፣ በአደባባዮቿም እስከ ሞት ቈስለው ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፥ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተገደሉት በከለዳውያን ምድር ይወድቃሉ፤ የቈሰሉትም በውጭ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፥ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉ። |
አንተ ግን ሳትቀበር በእግር እንደሚረጋገጥ የዛፍ ቅጠል የተጣልክ ሆነሃል፤ ሬሳህም በጦርነት ላይ በሞቱ ሰዎች ሬሳ ተሸፍኖአል፤ ከእነርሱም ሬሳ ጋር በድንጋያማ ጒድጓድ ውስጥ ተጥሎ ተረግጦአል።
በፈረሶቻቸው፥ በሠረገሎቻቸውና በቅጥር ወታደሮቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዝ! እነርሱም እንደ ሴቶች ይሁኑ፤ በሀብታሞቹ ላይ ሰይፍ መዛችሁ ሀብታቸውን ሁሉ ዝረፉ!