La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 51:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ እንደ እህል የሚያበጥሯትና ምድርዋን የሚያጠፉ የውጪ ጠላቶችን ወደ ባቢሎን እልካለሁ፤ እነርሱም የምትጠፉበት ጊዜ ሲደርስ ከየአቅጣጫው አደጋ ይጥሉባታል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲያበጥሯትና እንዲያወድሟት፣ ባዕዳንን በባቢሎን ላይ እልካለሁ፤ በመከራዋም ቀን፣ ከብበው ያስጨንቋታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በባቢሎንም ላይ የሚያዘሩትን ሰዎች እልካለሁ እነርሱም ያዘሩአታል፥ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፤ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በባ​ቢ​ሎ​ንም ላይ ተሳ​ዳቢ ሰዎ​ችን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይሰ​ድ​ቧ​ታል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባዶ ያደ​ር​ጋሉ፤ በመ​ከ​ራም ቀን በዙ​ሪ​ያዋ ይከ​ብ​ቡ​አ​ታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በባቢሎንም ላይ የሚያዘሩትን ሰዎች እሰድዳለሁ እነርሱም ያዘሩአታል፥ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፥ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 51:2
9 Referencias Cruzadas  

ወደ ሰማይ ትበትናቸዋለህ፤ ነፋስም ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእኔ በእስራኤል ቅዱስም ትመካለህ።


አዳኛችሁ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ የሚዘምት ሠራዊት እልካለሁ፤ የከተማዋን ቅጽር በሮች እሰባብራለሁ፤ የባቢሎናውያንም ፉከራ ወደ ለቅሶ ይለወጣል።


ገለባ በነፋስ እንደሚበተን፥ በምድሪቱ ውስጥ ባሉት ከተሞች ሁሉ በተንኳችሁ፤ ከክፉ ሥራችሁም ካለመመለሳችሁ የተነሣ፥ እናንተን ሕዝቤን አጠፋኋችሁ፤ ልጆቻችሁ ሁሉ እንዲገደሉ አደረግሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀስት መደገን የሚችሉትን ቀስተኞች በባቢሎን ላይ ይዘምቱ ዘንድ ጥሩአቸው፤ ከተማይቱን ይክበቡ፤ ማንም እንዳያመልጥ ተጠባበቁ፤ የክፉ ሥራዋንም ዋጋ ክፈሉአት፤ በሌሎች ላይ የፈጸመችውንም ግፍ በእርስዋም ላይ ፈጽሙባት፤ እርስዋ በእስራኤል ቅዱስ በእኔ ላይ ተዳፍራለች፤


አንቺ ትዕቢተኛይቱ ተሰናክለሽ ትወድቂአለሽ፤ ደግፎ የሚያነሣሽም አይኖርም፤ ከተሞችሽን በእሳት አቃጥላለሁ፤ በዙሪያሽም ያለው ነገር ሁሉ ይደመሰሳል።”


ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።


እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”