ኤርምያስ 5:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳኝ ወፎችን ይዞ በወፎች ጎጆ እንደሚያሰፍር፥ እነርሱም ቤታቸውን ከብዝበዛ ባገኙት ሀብት ይሞላሉ፤ ብርቱዎችና ሀብታሞች የሆኑትም ስለዚህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወፎች እንደ ሞሉት ጐጆ፣ ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍ እንደሞላበት የወፍ ቀፎ፥ እንዲሁ ቤቶቻቸው በሽንገላ ተሞልቶአል፤ ስለዚህም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፤ በዚህም ከብረዋል ባለጸጎችም ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፥ እንዲሁም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። |
ስለዚህ የሕዝቡን መሪዎችና አማካሪዎች ወደ ፍርድ አቅርቦ እንዲህ ይላቸዋል፦ “የወይኑን አትክልት ቦታ ዘረፋችሁ፤ ከድኾች በተዘረፈው ሀብትም ቤታችሁን ሞላችሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው?
ነገር ግን ከግብጽ ምድር መርቼ ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በዳስ በዓል ጊዜ በድንኳን እንደምትኖሩ ዐይነት፥ እንደገና ተመልሳችሁ በድንኳን እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።
በዚያን ቀን በአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓት በቤተ መቅደሱ መድረክ ላይ እየዘለሉ የሚያመልኩትንና የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል በተገኙ ዕቃዎች የሚሞሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።”
ከፍ ባለ ድምፅም እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ ሆነች! የርኩሳን መናፍስት ማደሪያ ሆነች! የሚያጸይፉና የሚያስጠሉ ወፎች መጠለያ ሆነች!