ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለምንድነው? “ልብሴስ ተቀዶ የተደፈርኩት ስለምንድነው?” ብለሽ ብትጠይቂ፤ ይህ ሁሉ የደረሰብሽ ኃጢአትሽ እጅግ የከፋ በመሆኑ ምክንያት እንደ ሆነ ዕወቂ።
ኤርምያስ 5:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤርምያስ ሆይ! ሕዝቡ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ነገር ያደረሰብን ስለምድን ነው?’ ብለው በጠየቁህ ጊዜ ከእኔ ተለይተው በገዛ ምድራቸው ላይ ባዕዳን አማልክትን እንዳመለኩ ሁሉ፥ እነርሱም ራሳቸው የእነርሱ ባልሆነ አገር የባዕድ ሕዝብ አገልጋዮች መሆናቸው እንደማይቀር ንገራቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ይህን ሁሉ ነገር ለምን አደረገብን?’ ብለው ቢጠይቁ፣ ‘እኔን፣ እንደ ተዋችሁኝና በራሳችሁ ምድር ባዕዳን አማልክትን እንዳገለገላችሁ፣ እንደዚሁ የእናንተ ባልሆነ ምድር ባዕዳንን ታገለግላላችሁ’ ትላቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፦ “አምላካችን ጌታ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለምን አደረገብን?” ቢሉ፥ አንተ፦ “እንደ ተዋችሁኝ፥ በአገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳገለገላችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች ታገለግላላችሁ” ትላቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፥ “አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደረገብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋችሁኝ፥ በሀገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ ሀገር ለሌሎች ሰዎች ትገዛላችሁ” ትላቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፥ እናንተ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን? ብትሉ፥ አንተ፦ እንደ ተዋችሁኝ በአገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች ትገዛላችሁ ትላቸዋለህ። |
ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለምንድነው? “ልብሴስ ተቀዶ የተደፈርኩት ስለምንድነው?” ብለሽ ብትጠይቂ፤ ይህ ሁሉ የደረሰብሽ ኃጢአትሽ እጅግ የከፋ በመሆኑ ምክንያት እንደ ሆነ ዕወቂ።
ስለዚህ ከዚህች አገር አውጥቼ፥ እናንተም ሆናችሁ የቀድሞ አባቶቻችሁ ወደማያውቁት አገር እወረውራችኋለሁ፤ እዚያም ሐሰተኞች አማልክትን ቀንና ሌሊት ታመልካላችሁ፤ ፈጽሞ ምሕረት አላደርግላችሁም።’ ”
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
ሕዝቤ ሁለት ኃጢአት ሠርተዋል፤ ይኸውም የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተውኛል፤ ውሃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጒድጓዶችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።”
“እስራኤል የተገዛች ባሪያ አይደለችም፤ የቤት ውልድም ባሪያ አይደለችም፤ ታዲያ፥ ጠላቶችዋ (በምርኮ እንደ አውሬ የሚያድኑአት) ለምንድን ነው?
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ምድሪቱ ማንም ሊዘዋወርባት የማይችል ደረቅ በረሓና ጠፍ መሆንዋ ስለ ምንድን ነው? ይህንንስ የሚያስተውል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? ለሌሎች ማስረዳት ይችል ዘንድ የገለጥክለትስ ማን ነው?”
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው ሕዝቤ እኔ የሰጠኋቸውን ሕግ በመተዋቸው ነው፤ እነርሱ ለእኔ አልታዘዙም፤ የነገርኳቸውንም ሁሉ አልፈጸሙም።