ኤርምያስ 49:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሣቸውንና መሪዎቻቸውን አጠፋለሁ፤ ዙፋኔንም በዚያ እዘረጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዙፋኔን በኤላም እዘረጋለሁ፤ ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠፋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዙፋኔንም በኤላም አኖራለሁ ከዚያም ንጉሡንና ሹማምንትን አጠፋለሁ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዙፋኔንም በኤላም አኖራለሁ፤ ከዚያም ንጉሡንና መሳፍንቱን አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዙፋኔንም በኤላም አኖራለሁ ከዚያም ንጉሡንና አለቆቹን አጠፋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ከዚያም የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አገልጋዬ የሆነውን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ወደዚህ ስፍራ አምጥቼ አንተ በቀበርካቸው በእነዚያ ድንጋዮች ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ የቤተ መንግሥት ድንኳኖቹን የሚተክልባቸው መሆኑን ንገራቸው።
የዔላም ሕዝብ ሕይወታቸውን ሊያጠፉ የሚፈልጉትን ጠላቶቻቸውን እንዲፈሩ አደርጋለሁ። በእነርሱም ላይ ለጥፋታቸው ምክንያት የሆነው ኀይለኛ ቊጣዬን አመጣባቸዋለሁ፤ እስኪያልቁ ድረስ በጦርነት እንዲሳደዱ አደርጋለሁ።