ኤርምያስ 48:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዝናዋን የምታውቁና በአቅራቢያዋ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ‘የሥልጣን ምልክት የሆነው የተከበረው ኀይልዋ፥ በትረ መንግሥትዋ እንዴት ተሰበረ’ በማለት ዋይ! ብላችሁ አልቅሱላት! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤ ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤ ‘ብርቱው ከዘራ፣ የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ብርቱው በትረ መንግሥት፥ የከበረው ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ!፥ ብላችሁ አልቅሱለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠንካራውም ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ብርቱው በትር፥ የከበረው ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት። |
የሀሴቦን እርሻዎችና የሲብማ የወይን ተክል ቦታዎች ተደምስሰዋል፤ እነዚህ የወይን ተክል ቦታዎች የአሕዛብ መሪዎችን የሚያሰክር የወይን ጠጅ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ነበሩ፤ ከዚያ በፊት የእነዚያ የወይን ተክሎች ሐረግ እስከ ያዕዜር ከተማ ድረስ የተንሰራፋ ነበር፤ እንዲሁም በስተ ምዕራብ እስከ ሙት ባሕር ማዶና በስተ ምሥራቅም እስከ በረሓው ይደርስ ነበር።
በቀድሞ ዘመን ምድያማውያንን ድል እንዳደረግህ ሁሉ፥ አሁንም በሕዝብህ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበርና በትከሻቸው ላይ የተቃጣውን በትር ሰባበርክ፤ ሕዝብህን በማስጨነቅ ይገዛ የነበረውን ድል አደረግህ።
በሞአብ ላይ ምን ዐይነት አስደንጋጭ ሁናቴ ደርሶ ነው የምታለቅሰው? እንዴትስ በዕፍረት ጀርባዋን ትሰጣለች? ስለዚህም ለጐረቤቶችዋ ሁሉ መሳለቂያና አስደንጋጭ ሆናለች።”