በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።
ኤርምያስ 4:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድርን ተመለከትኩ፤ እነሆ ባድማ ሆናለች፤ ሰማይንም ተመለከትኩ፤ እነሆ ብርሃን አይታይበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርን ተመለከትሁ፤ እነሆ ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች፤ ሰማያትንም አየሁ፣ ብርሃናቸው ጠፍቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱን ተመለከትሁ፤ እነሆም ባዶ ነበረች፤ ሰማያትንም ተመለከትሁ፤ ብርሃንም አልነበረበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፥ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም። |
በዚያን ጊዜ ምድር ቅርጽ የሌላትና ባዶ ነበረች፤ ጨለማም በጥልቁ (ውቅያኖስ) ላይ ነበር፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ይሰፍ ነበር።
በዚያን ቀን እንደ ባሕር ማዕበል እየተመሙ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ይመጡባቸዋል፤ እነሆ ወደ ምድር ቢመለከቱ በጨለማና በመከራ እንደ ተከበቡ ያያሉ፤ ከደመናውም የተነሣ ብርሃኑ ይጨልማል።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሁሉም ወና ስለ ሆኑና በእነርሱም ላይ የሚዘዋወርባቸው ስለሌለ፥ ስለ ተራራዎች አዝናለሁ፤ ስለ ሜዳዎችም አለቅሳለሁ፤ የከብቶች ድምፅ ዳግመኛ አይሰማም፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ሁሉ ሸሽተው ጠፍተዋል።”
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።