“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤
ኤርምያስ 4:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝብዋ በእግዚአብሔር ላይ ስለ ዐመፁ፥ እንደ መከር እህል ጠባቂ ኢየሩሳሌምን ጠላት ይከባታል፤” ይህን የተናገረ እግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰብል እንደሚጠብቁ ሰዎች ይከቧታል፤ በእኔ ላይ ዐምፃለችና፤’ ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ሆነውባታል፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔ ላይ ዐመፀኛ ሆናለችና በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ሆነውባታል” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ሆነውባታል፥ ይላል እግዚአብሔር። |
“ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤
አንተም ለብዙ ዓመቶች ታገሥካቸው፤ ያስተምሩአቸውም ዘንድ ነቢያትን በመንፈስህ አስነሣህላቸው፤ ነገር ግን እነርሱ አላዳመጡም፤ ስለዚህም ለጐረቤት ሕዝቦች ድል እንዲነሡአቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊቱን ሁሉ አስከትቶ በመምጣት በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል አስከበባት፤ ሠራዊቱም በከተማይቱም ዙሪያ ሰፈረ፤ በቅጥሩም ዙሪያ ዐፈር ቈለለ።
“በትእዛዙ ላይ ያመፅሁ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔር ባደረገው ነገር እውነተኛ ነው፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ አድምጡ ሥቃዬንም ተመልከቱ፤ ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ተማርከው ተወስደዋል።
ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ሠርታለች፤ መሳለቂያም ሆናለች፤ ዕርቃንዋን ስላዩአት የሚያከብሩአት ሁሉ ይንቁአታል፤ እርስዋ ራስዋ እየቃተተች ፊትዋን ታዞራለች።