ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።
ኤርምያስ 35:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ፣ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ የሚል ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እንዲህ ሲል፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ |
ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።
እንዲሁም የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠበት ዘመንና፥ ከዚያም በኋላ የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ነግሦ ዐሥራ አንድ ዓመት እስከሆነው ድረስ ማለት በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ተወሰደ ድረስ የእግዚአብሔር ቃል በኤርምያስ አማካይነት ተነግሮአል።
የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ተናገረኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ነበር፤
የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በይሁዳ እንደ ነገሠ ወዲያውኑ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቆመህ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለስግደት ወደዚያ ለሚመጡት ሕዝብ እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ አንድ ነገር እንኳ ሳታስቀር ንገራቸው።
ለንጉሡም እንዲህ ብዬ እንድነግረው አዘዘኝ፦ “እነሆ አንተ የብራናውን ጥቅል አቃጥለሃል፤ ‘የባቢሎን ንጉሥ መጥቶ ይህችን ምድርና በእርስዋ የሚኖሩትን ሕዝብ፥ እንዲሁም እንስሶችን ሁሉ እንደሚያጠፋ ትንቢት የተናገርከው ስለምንድን ነው?’ ብለህ ኤርምያስን ጠይቀኸዋል፤
የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብና ከይሁዳ ከተሞች የመጡት ሕዝብ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ለማግኘት የጾም ጊዜ አወጁ።