ኤርምያስ 34:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እኔ እግዚአብሔር እናንተንም የምላችሁ ይህ ነው፦ ‘አልታዘዛችሁም፤ ወገኖቻችሁ ለሆኑ እስራኤላውያንም ነጻነት አልሰጣችሁም፤’ ስለዚህም እኔ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ ትሞቱ ዘንድ እተዋችኋለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገውም ነገር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለወንድሞቻችሁና ለወገኖቻችሁ ነጻነት አላወጃችሁምና አልታዘዛችሁኝም። እንግዲህ እኔ ነጻነት ዐውጅላችኋለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር። ‘ይኸውም በሰይፍ፣ በቸነፈርና በራብ የምትወድቁበት ነጻነት ነው። ለምድር መንግሥታት ሁሉ መሠቀቂያ አደርጋችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው ዓመተ ኅድገትን ለማድረግ እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር፥ ለራብም ዓመተ ኅድገትን አውጅባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እበትናችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፥ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እንድትበተኑ አደርጋችኋለሁ። |
‘ታዲያ ወዴት እንሂድ?’ ብለው ቢጠይቁህ፥ ከዚህ በፊት እንዲህ ብዬ የነገርኳቸውን አስታውሳቸው፤ ‘በመቅሠፍት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በመቅሠፍት ይሞታሉ! በጦርነት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በጦርነት ይሞታሉ! በራብ እንዲሞቱ የተፈረደባቸውም በራብ ይሞታሉ። ተማርከው እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ወደ ምርኮ ይሂዱ።’
የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በይሁዳ በነገሠበት ዘመን በኢየሩሳሌም ስለ ፈጸመው ክፋት ሁሉ በእነርሱ ላይ ከሚደርሰው ነገር የተነሣ የዓለም ሕዝብ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ።”
አንተና መኳንንትህ ከወረርሽኝ፥ ከጦርነትና ከራብ የሚተርፉትንም ሕዝብ በሙሉ በንጉሥ ናቡከደነፆርና ሊገድሉህ በሚፈልጉህ ጠላቶችህ እንድትማረኩ አደርጋለሁ፤ እርሱም ምሕረት ወይም ርኅራኄ በማሳየት አንድ ሰው እንኳ አይተውልህም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ በእነርሱ ላይ ጦርነትን፥ ራብንና ቸነፈርን ላመጣባቸው ነው፤ ከመበላሸቱ የተነሣ ሊበሉት እንደማይቻል የበለስ ዛፍ ፍሬ አደርጋቸዋለሁ፤
በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር አባርራቸዋለሁ፤ የዓለም ሕዝብ ሁሉ በእነርሱ ላይ ስለሚያዩት ነገር ይደነግጣሉ፤ እንዲበተኑ በማደርግበት ስፍራ ሁሉ በእነርሱ ላይ የማደርሰውን ነገር የሚያዩ ሕዝቦች ሁሉ በመደንገጥ ይሸበራሉ። ሕዝብም ሁሉ መሳቂያና መሳለቂያ ያደርጋቸዋል።
“እነሆ ባቢሎናውያን ከተማይቱን ለመያዝ ዐፈር ቈልለው ዙሪያዋን በመክበብ ላይ ናቸው፤ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር ከተማይቱ በእነርሱ እጅ እንድትወድቅ ያደርጓታል፤ እነሆ አንተ የተናገርከው ሁሉ መድረሱን ታያለህ፤
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ኤርምያስ ሆይ! እነሆ ሕዝቡ ‘ይህችን ከተማ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር በባቢሎን ንጉሥ እጅ እንድትወድቅ ሊያደርጉአት ነው’ ይላሉ፤ እነሆ እኔ የምለውን ሌላ ነገር ደግሞ ስማ፤
የባሪያ ነጻነትን ለማወጅ ሴዴቅያስ ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ጋር ተሰብስቦ ስምምነት ካደረገ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ ወደ ኤርምያስ መጣ።
የተናገርኩትም ቃል ይህ ነበር፦ “በከተማይቱ የሚቀሩ ሁሉ በጦርነት፥ በረሀብ ወይም በወረርሽኝ ይሞታሉ፤ ወደ ባቢሎናውያን ሄዶ እጁን የሚሰጥ ግን አይገደልም፤ እርሱ ሕይወቱን ለማትረፍ ያመልጣል።”
ኢየሩሳሌም ከባድ ኃጢአት ሠርታለች፤ መሳለቂያም ሆናለች፤ ዕርቃንዋን ስላዩአት የሚያከብሩአት ሁሉ ይንቁአታል፤ እርስዋ ራስዋ እየቃተተች ፊትዋን ታዞራለች።
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤
“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።